እጅ በእጅ ገበያ
Eji Be Eji Marketplace
እጅ በእጅ ገበያ

ገበያው በእጅዎ ላይ ነው!

የእጅ በእጅ ገበያ ዋና ዓላማ ገበያውን ለሁሉም ተደራሽ፣ ቀልጣፋ እና ባለብዙ አማራጭ ማድረግ ነው። በተጨማሪም አላስፈላጊ እንግልትንና ወጪን ማስቀረት ላይ ያተኩራል። እጅ በእጅ ገበያ የሚፈልጉትን ዕቃ በቀላሉ የሚሸጡበትና የሚገዙበት፣ በርካታ አማራጮችን አይተው ዋጋ አወዳድረው የሚገበያዩበት ዘመናዊ መድረክ ነው።

Eji Be Eji Marketplace • Ethiopia's direct marketplace for goods, jobs and services

ለግለሰቦች

ማንኛውንም ያገለገለ ወይም አዲስ ዕቃ መሸጥ ከፈለጉ እጅ በእጅ ገበያ በእጅዎ ላይ ይገኛል። በስልክዎ ወይም በኮምፒውተርዎ አካውንት በመክፈት የሚሸጡትን ዕቃ ይልቀቁ፤ ገዢዎች በሰከንዶች ውስጥ ያገኙዎታል። ለመግዛትም እንዲሁ ገበያው ውስጥ በመግባት የሚፈልጉትን ዕቃ ይፈልጉ፤ ከሻጩ ጋር በሚመችዎት መንገድ ተገናኝተው ይገበያዩ።

ለነጋዴዎች

በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን ንግድዎን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግሩ! የሚሸጡትን ማንኛውንም ምርት በእጅ በእጅ ገበያ ላይ በቀላሉ በመለጠፍ በሺዎች የሚቆጠሩ ደንበኞችንና ገዢዎችን በቅጽበት ያግኙ።

እጅ በእጅ ገበያ — ቀላል፣ ቀልጣፋ፣ ፈጣን እና ዘመኑን የዋጀ!

የአጠቃቀም ሂደት

መለያ → ማረጋገጫ → ቀጥተኛ ውይይት

1መለያ ይክፈቱ
2ስልክዎን በቴሌግራም ያረጋግጡ
3ልጥፍ ይለጥፉ ወይም ይፈልጉ
4ያለ ደላላ በቀጥታ ተስማምተው ይገበያያሉ

የተረጋገጡ ሻጮች

ከመለጠፍ በፊት በቴሌግራም የተረጋገጠ ስልክ

ነጻ ቀጥተኛ ውይይት

ገዢና ሻጭ በቀላሉ ይገናኛሉ

ዝቅተኛ ዳታ ሁኔታ

ለዝግ ኢንተርኔት የተሰራ

ሞባይል መጀመሪያ

ለትንሽ ስክሪኖች በተለይ የተዘጋጀ

እጅ በእጅ

አምስቱ የእጅ በእጅ መርሆዎች

ዋና ዓላማችን አላስፈላጊ እና አሰልቺ ውጣ ውረድ የበዛባቸውን የደላላ ሂደቶች በመቀነስ፣ የጊዜና የገንዘብ ብክነትን ማስቀረት፤ እንዲሁም ማህበረሰቡ በቀጥታ ተገናኝቶ ቀልጣፋ የገበያ ሥርዓት እንዲያገኝ ማድረግ ነው።

ቀለል ያለ

Simple

ማንኛውም ሰው በቀላሉ ሊጠቀመው የሚችል፣ ግልጽ እና ምቹ አቀራረብ።

ቀልጣፋ

Efficient

ያለ አላስፈላጊ ውጣ ውረድ ገዢና ሻጭን ወይም አጣሪና አገልግሎት ሰጪን በቀጥታ የሚያገናኝ።

ፈጣን

Fast

በደቂቃዎች ውስጥ ዕቃዎችን ለመሸጥ፣ ሥራ ለመቀጠር ወይም አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችል ፍጥነት።

ነፃ

Free

ያለ ምንም የተደበቀ ክፍያ ወይም ከፍተኛ ኮሚሽን የሚሰጥ ነፃ አገልግሎት።

ያለ ደላላ

Direct

ከመካከለኛ ወኪሎች ነፃ የሆነ፣ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረግ ቀጥተኛ ስምምነት።

የተደገፈ ማስታወቂያTEXT

ምርትዎን ወይም አገልግሎትዎን ያስተዋውቁ

በእጅ በእጅ ገበያ ውስጥ በገበያና በይሽጡ ገጾች ላይ የሚታይ ማስታወቂያ ይጀምሩ።

እይታ 0ልዩ እይታ 0ተደጋጋሚ 0

ምርትዎን ያስተዋዉቁ

ምድቦች

በምድብ ይፈልጉ

ገበያ

በቅርብ የተለጠፉ እቃዎችና አገልግሎቶች

ተጨማሪ

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ምን ማድረግ ይችላሉ?

የዕቃዎች ገበያ

አዳዲስና የተጠቀሙባቸውን የቤት፣ የመስሪያ ቤት እና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በቀጥታ መሸጥና መግዛት።

የሥራ ዕድልና አገልግሎት

ሥራ ፈላጊዎችና አሠሪዎች፣ እንዲሁም የሙያ አገልግሎት ሰጪዎችና ፈላጊዎች በቀጥታ የሚገናኙበት መድረክ።

ምቹ የዲጂታል አማራጭ

ወደ ገበያ መሄድ ሳይጠበቅብዎ በሞባይል ስልክዎ ወይም በኮምፒውተርዎ ሁሉንም ፍላጎቶችዎን በቦታው ሆነው ማከናወን።

ለምን እጅ በእጅ ገበያ ይመረጣል?

  • ፈጣን፣ ቀለል ያለ፣ ብቃቱን ያረጋገጠ እና መልካም ተፅዕኖ ያለው አገልግሎት መስጠት።
  • የሀገራችንን የአገልግሎት ውጣ ውረድ እና የሀብት ብክነት መቀነስ።
  • የደላሎችን አላስፈላጊ ሰንሰለት በቁርጠኝነት መስበር።
  • ገበያተኞችን ከሽያጭ፣ አገልግሎት ፈላጊዎችን ከአገልግሎት ሰጪዎች፣ እንዲሁም ሻጮችን ከገዢዎች ጋር በማገናኘት የሚያስፈልጋቸውን ሰጥተው የሚፈልጉትን እንዲያገኙ ማድረግ።
  • ያለ አላስፈላጊ የኮሚሽን ክፍያ እና የደላላ ውጣ ውረድ፤ ወደ ገበያ በአካል መሄድ ሳይጠበቅብዎት በስልክዎ ወይም በኮምፒውተርዎ ላይ ሆነው የሚፈልጉትን ሁሉ ማግኘት።